Seal An official website of the Ewketle Limat
Training Program

ለፓራዳይዝ ትምህርት ቤቶች መምህራን የተሳካ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

በእውቀት ለልማት ኃ/የተ/ ሁለገብ ህብረት ስራ ማህበር ስር ለሚተዳደሩት የፓራዳይዝ ትምህርት ቤቶች መምህራን በቀን 19/07/2018 ዓ.ም የተሳካ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።

ይህ ስልጠና የተሰጠው በማህበሩ ምክትል ሰብሳቢ በአቶ አምበሉ አበበ እና የቁጥጥር ኮሚቴ ሰብሳቢ በሆኑት በአቶ ሙሉ ደስታ አሰልጣኝነት ነው። ስልጠናው በመማር ማስተማር ሂደቱ እጅግ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ማለትም፤ በማስተማሪያ ዘዴ ዝግጅት፣ በክፍል አያያዝ፣ እንዲሁም በፈተና አዘገጃጀትና አተገባበር ዙሪያ በሰፊው ትኩረት አድርጎ የተሰጠ መሆኑ ታውቋል።

ይህ ስልጠና ማህበሩ ለአካባቢው ማህበረሰብ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በመስጠት በስነምግባር የታነጸ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት፣ እንዲሁም በክልሉ ቀዳሚ እና ተመራጭ የትምህርት ተቋም ለመሆን የያዘውን ራዕይና ተልዕኮ ከዳር ለማድረስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

Return to the Briefing Room to view all updates.

View All News